Textruta: Textruta: ንጋት
Textruta: ስደት

Textruta:  
 
ዋና ገጽ
 
ዜና
 
ርዕሰ አንቀፅ
 
አስተያየት - ትችት
 
ፖለቲካ
 
ማኅበራዊ
 
ኪነጥበብ
 
ስደት
 
አስፈንጣሪች
 
ጠቃሚ ሣይቶች
 
ስለእኛ
 
አድራሻችን
 
 
 
 
ምሉዕ የአማርኛ፣ የትግርኛና የግዕዝ ሶፍት ዌር 
ምስጋና ለፀጋዬ ገብራይ

 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Textruta: ከ፦ስደተኛው - ፬፦ የቤተሰብ ፍቅር 
ያሬድ ክንፈ ከስዊድን (የንጋት ዋና አዘጋጅ) 
እንደምን ከረምክልኝሳ ጌትዬ? እኔ አንድዬ የተመሰገነ ይሁን እተነፍስልሃለሁ። ‘ናፍቆት’ አይገባኝም ነበርና ’ባክህ። እኔና አንተ ብዙም ልዩነት እንደሌለን እርግጥ ነውና በል እንግዲህ አድምጠኝማ። 
“ምን ናፈቀህ?” ብለህ ብትጠይቀኝ “ያልናፈቀኝን ጠይቀኝ” የሚል ነው ምላሼ። ካገርህ ስትወጣ አገርህ፣ ቤተሰብህ፣ ጓደኞችህ፣ … ብቻ አይደለም የሚናፍቁህ አየሩ ሁሉ ሳይቀር ይናፍቅሃል። ስንቱን ዘርዝሬ እንደምጨርስልህ ባላውቅም እስቲ ልሞክር። 
ሃያ አንደኛዋ የቤት አከራዬ ወ/ሮ ጣይቱን አስታወስካቸው? ለቤት ኪራይ የከፈልኳቸው ገንዘብ ወሩ አጋማሽ ላይ ስታልቅባቸው ነው መሰል በገባሁ በወጣሁ ቁጥር የሚነዘንዙኝና በነገር ጠቅ የሚያደርጉኝ፣ ያቺ ነገረኛና ባለአለብላቢት ምላሳሟ ያንተ የቤት አከራይ፣ እኛ “ማታ ማታ ወይም ጠዋት ጠዋት ካልሆነ ውሃ መቅዳት አትችልም፤ ሊያውም አንድ ባልዲ” ይሉኝ የነበሩት የመጀመሪያው የቤት አከራዬ - አቶ አበበ፣ በየተከራየሁባቸው አርባ ሦስት ቤቶች አካባቢ ያሉ ባለሱቆች፣ ብድር ይከለክሉኝና ይሰጡኝ የነበሩት ባለሱቆች፣ “ሽንት ቤት ብዙ ትጠቀማለህ፣ በዚህ ላይ ጓደኞችሁ ሁሉ በመጡ ቁጥር ሽንት ቤት ሳይገቡ አይሄዱም” ብለው ከቤታቸው ያስለቀቁኝ ሰላሳኛው የቤት አከራዬ፣ “ጓደኛ ታበዛለህ” - “አምሽተህ ትገባለህ” - “ስትወጣና ስትገባ ሠላም አትለኝም” - “ስትወጣና ስትገባ አትታይም” - “የግል ጋዜጣ ላይ እንደምትሠራ ለምን አልነገርከኝም” - “የግል ጋዜጣ ታነባለህ” - “ከምሽቱ አራት ሰዓት በኋላ መብራት ለምን ታበራለህ?” … ብለው እያሉ ከቤታቸው ያስለቀቁኝ የቤት አከራዮቼ ሁሉ ናፍቀውኛል። ጓዴ በ’ናትህ አጠገባቸው እስካለህ ድረስ ምን ቢበድሉህ፣ ቢያስቀይሙህና ቢጠሉህ፤ አንተ ግን ውደዳቸው። እንደኔ ከተሰደድህ የነሱ ሁሉ ናፍቆት አያስቀምጥህምና። ... .ሙሉውን አስነብበኝ
ከ፦ስደተኛው - ፫፦ ኃይማኖት 
ያሬድ ክንፈ - ከስዊድን (የንጋት ዋና አዘጋጅ) 
ጌትዬ! እንደምን አለህልኝ ባክህ? ወዳጆቻችን፣ ዘመዶቻችን፣ ባልንጀሮቻችን፣ ጓዶቻችን፣ … ወገኖቻችን እንዴት እንዴት ይዟቸዋል? ላንዳቸውም ሳታዳላ የተለመደ ሠላምታዬን አድርስልኝ - እባክህ! 
እዚህ ክረምቱ ገብቶ አበሳዬን እያየሁልህ ነው። የአዲስ አበባ ክረምት ምን አላትና!? በረዶው እንደጨው ተከምሮ ንጣቱ ሲያምር ልነግርህ አልችልም። ፊልም ላይ ያየሁትን በእውኔ አየሁት። ጠኃይቱ በ፳፬ (24) ሰዓት ውስጥ ስድስት ሰዓት ለማይሞላ ጊዜ ታያታለህ። እሱንም በጉም ካልተሸፈነች። ፲፰ (18) ሰዓቱ ግን ድቅድቅ ጨለማ ነው። ጠዋት ከሁለት ሰዓት በፊት አታያትም። ቀን ወደ ስምንት ሰዓት አካባቢ ትጠልቃለች።  ወደ ሰሜን ስዊድን ስትሄድ ደግሞ ግፋ ቢል ሁለት ሰዓት ያህል ጊዜ ጠኃይቱን የማየት ዕድል ሊገጥምህ ይችላል። የቀረው ሃያ ሁለት ሰዓት ጨለማ መሆኑን አትዘንጋ።ጠኃይቱ ፏ ብላ እያየሃት ውጪ ወጥተህ ልትሞቃት ስትሞክር ብርዱ ጠብሶህ ወደ ቤትህ ትገባለህ። አርቴፊሻል ነች ማለቱ ይቀላል። ካልክስ ቤትህ ውስጥ ሆነህ በመስኮት ከገባች ትንሽ ሙቀትዋ ይሰማሃል። ... ሙሉውን አስነብበኝ
ከ፦ስደተኛው - ፪፦ ሥራ 
ያሬድ ክንፈ ከስዊድን (የንጋት ዋና አዘጋጅ) 
እንዴት ነህ ’ባክህ ጌታው? ወዳጆቻችንስ እንዴት ናቸው? … እኔ አማን ነኝ። የስደት ሕይወት ባይጣፍጥም እየኖርኩት ነው። ከእርግማን ባትቆጥርብኝ ”ከስደት ይሰውርህ!” ብዬ ብመርቅህ ወደድሁ። ፭ (5) እና ፲ (10) ዓመት እዚህ ስቆይ ”ለስደት ይዳርግህ!” እንደማልልህ ግን እርግጠኛ አይደለሁም። 
እዚህ ከመጣሁ ከተገረምኩባቸው ነገሮች አንዱ ”ሥራ” ነው። የፈለግህበት የመንግሥትም ሆነ የግል መስሪያ ቤት፣ ቢሮ፣ ሱቅ፣ ሱፐር ማርኬት፣ ሆስፒታል፣ መዝናኛ ቦታ፣ … ስትሄድ እንዴት ያለ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንደሚሰጡህ ልነግርህ አልችልም። ከምነግርህ በላይ ረክተህ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉዳይህን ፈጽመህ፣ ሳትጉላላ፣ ቢሮክራሲ ሳይጫንህ - ሳይገላምጥህ - ሳያንጓጥጥህ፣ የምትሻውን አግኝተህ፣ … ወደቤትህ ትመለሳለህ። አንድ ጉዳይ ቢኖርህ የግድ እዚያ መስሪያ ቤት መሄድ የለብህም። የፈለግህበት ሆነህ ስልክ ደውለህ ወይም በኢንተርኔት ጉዳይህን ታስፈጽማለህ። የምትገዛው ነገርም ቢሆን እቤትህ ሆነህ ትገዛዋለህ። የገዛኸው ነገር በርህን አንኳኩቶም ይሁን ሳያንኳኳ ቤትህ ድረስ ይመጣልሃል። ... ሙሉውን አስነብበኝ
ከ፦ስደተኛው - ፩፦ እህልና እኛ
ያሬድ ክንፈ - ከስዊድን (የንጋት ዋና አዘጋጅ)
እንደምን አለህማ ወዳጄ ሆይ? አዲስ መዲናችን እንዴት ነች? እንደአዲስ ሊሠሯት ሩጫ ላይ መሆናቸውን ሰማሁ። እንዳንተው ወሬኛም አይደለሁ?! ወሬ አያመልጠኝም ማለት ትችላለህ - ዕድሜ ለኢንተርኔት! ከነፃው ፕሬስ፣ ከኢህአዴግ ሚዲያዎች፣ በውጭ አገር ከሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች፣ ከውጭ ሚዲያዎች፣ … ከተገኘው ሁሉ ወሬ እለቃቅማለሁ። ሁሉንም ከኢንተርኔት ነው የማገኘው። ቢቢሲ ቴሌቭዥንንም አልፎ አልፎ ለዓለም ወሬ እከታተላለሁ። ሠላምታዬን ሳልጨርስ ወሬዬ ላይ ተዘረፈጥኩማ። ኧረ! ወዳጆቻችንና ጓዶቻችን እንዴት ናቸው ባክህ? አዲስ አበባ ሬስቶራንት፣ ጊዮርጊስ፣ ካዛንችስ፣ ዑራዔል፣ ፒኮክ ጀርባ፣ ኦሎምፒያ፣ ፍላሚንጎ፣ ቦሌ - ብርሐንና ሠላም - አርቲክራፍት - ... ማተሚያ ቤቶች፣ አራት ኪሎ፣ … ያሉቱን ለአንዳቸውም ሳታዳላ የከበረ ሠላምታዬን አድርስልኝ - እባክህ! 
ጌታው! ሥራ እንዴት ነው? የቢሮህ ሰዎችስ ሠላም ናቸው? አንተ ቢሮ እየመጣሁ የምጠጣው ቡና እንዴት ናፍቆኛል መሰለህ! እዚህ ከመጣሁ አፌን ሞልቼ ”ቡና ጠጣሁ!” ያልኩበት ቀን የለም። ጎረቤትህ የእሙዬ እናት የሚያፈሉት ቡና ሦስተኛው እዚህ ስዊድን ካሉት ካፌዎች አንዱ ጋር ገብተህ በ፲፰ (18) ክሮነር ገዝተህ ከምትጠጣው ይሻላል። (አንድ የስዊድን ክሮነር ከኢትዮጵያው አንድ ብር ጋር ተቀራራቢ ነው)። እዚህ ያለውን ኑሮ ከኢትዮጵያ ጋር ካወዳደርከው ቢያንስ ከኢትዮጵያ በስምንት እጥፍ ይወደዳል። አማካኙን ከወሰድከው በአስር እጥፍ ማለት ትችላለህ። አብዛኛው ነገር ከኢትዮጵያ ይወደዳል። ከኢትዮጵያ የሚቀንስም፣ እኩል የሆነም ነገር አለ፤ ግን ብዙ አይደለም። የኑሮው ውድነት የሚካካሰው በሰዉ ገቢ ነው። ገቢው የዚያኑ ያህል ዳጎስ ያለና ከኢትዮጵያ ጋር ስታወዳድረው በትንሹ ፲፭ (15) እጥፍ ይበልጣል። ከ፳፭ (25) እጥፍ የሚበልጥበት ጊዜም አለ። ሥራ-አጥ ስዊድናዊ ወይም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ካለህ መንግሥት እየደጎመህ ትኖራለህ። በስዊድንኛ ”ቢድራግ” ይባላል። እንዲያም ሆኖ ሰዉ የሥራ ፍቅሩን ልነግርህ አልችልም። ቁጭ ብሎ ቢድራግ እየበላ የሚኖር ከስንት አንድ ነው። ይህ ገንዘብ (ቢድራጉ) የሚመጣው ከህዝብ ላይ ከሚቆረጥ ቀረጥ ነው። ብዙ ከሠራህና ደምወዝህ ከፍ ካለ፤ የምትከፍለው ግብር (ቀረጥ) የዚያኑ ያህል ይጨምራል። ... ሙሉውን አስነብበኝ

 

 

 

 

Hosted by www.Geocities.ws

1