Textruta: Textruta: ንጋት
Textruta: ማኅበራዊ

Textruta:  
 
ዋና ገጽ
 
ዜና
 
ርዕሰ አንቀፅ
 
አስተያየት - ትችት
 
ፖለቲካ
 
ማኅበራዊ
 
ኪነጥበብ
 
ስደት
 
ሊንኮች
 
ጠቃሚ ሣይቶች
 
ስለእኛ
 
አድራሻችን
 
ለፈገግታ 
 
 
ምሉዕ የአማርኛ፣ የትግርኛና የግዕዝ ሶፍት ዌር 
ምስጋና ለፀጋዬ ገብራይ

 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Textruta: ከድክመቶቻችን ጀርባ የቆመው ማነው? 
ፀዳለ ክፍሌ 
በትራፊክ አደጋ ብዛት ከዓለም ስንተኛ እንደሆንን እንደ በጐ ነገር ደግሜ አልናገረውም። ይሁን እንጂ በምን ምክንያት እንዲህ "እንዳሻቀብን" መጠየቅ አግባብ ይሆናል። ብዙ ነገሮች ልብ ብለው ሲያስተውሏቸው ለዘመናት በምክንያትነት ሲደረደሩ የኖሩ ጉዳዮች አንዳንዴ ባዶ ናቸው ባይባልም ዋናው ምክንያት እየተረሳ በቅብብሎሽ ሲወተወቱ የኖሩ መሆናቸው ይገባናል። ለትራፊክ አደጋ መፈጠር ዋና ዋና ተብለው ሲጠቀሱ የኖሩና ያሉ ምናልባትም ዓለማቀፍ ይዘት ያላቸው ነጥቦች አሉ። "ከጠጡ አይንዱ - ከነዱም አይጠጡ" ከሚለው ማስጠንቀቂያ ጀምሮ የመኪናውን ሙሉ አካል ጤነኛ መሆኑን ማረጋገጥ ይመከራል። አሽከርካሪዎች ከሃሺሽና ጫትን ከመሳሰሉ አደንዛዥ ዕፆች እንዲርቁም ከምክር አልፎ በሕግ እስከማገድም ተደርሷል። 
የየአገሮች ሁኔታ የተለያየ ቢሆንም የመንገዶች ጥበትና የተሽከርካሪ ብዛትም ለአደጋ ምክንያት ይሆናል። የመንገድ ምልክቶችና መብራቶችም በተገቢው መሥራት አግባብ መሆኑ ይታመናል። ተገቢ ባልሆነ ቦታ ከተገቢው በላይ መብረር፣ በኩርባ መንገድ ላይ ፍጥነትን አለመቀነስና ባልተመቸ ቦታ ተሽከርካሪን መቅደም የአደጋ መንስዔ ሊሆን ይችላል ... ... ሙሉውን ፅሁፍ አስነብበኝ
የሚሸጡ ልጆች 
ፀዳለ ክፍሌ (የንጋት ባልደረባ) 
ልጆች ወልደዋል? ደሃ ነዎት? ታዲያ ለምን አይሸጧቸውም? እውነቴን’ኮ ነው። በተለይ ቀላ ብለው ድንቡሽቡሽ ያሉ ከሆኑ የደራ ገበያ አለ። የኔ ነገር ወሬውን አጋጨሁት መሰለኝ። ልጅ የሚያሸጥ ድህነት ላይ ከተደረሰ ልጁ ድንቡሼ ሊሆን እንደማይቻል ዘነጋሁት። ሰው ኑሮውን ነዋ የሚመስለው። ክፋቱ ደግሞ ዝንብ የወረረውና የሽሮ ቅል የመሰለ ልጅ ለገበያ አይመችም። ቆንጆም ቢሆን ጥቁር ከሆነ አይድከሙ። እርሶስ ቢሆን በግ እንኳን ሲገዙ ምን ቢሰባ ጥቁር ከሆነ ገሸሽ ያደርጉት የለ። እውነቴን’ኮ ነው የጥቁር በግ ዋጋ’ኮ ይቀንሳል። ስለዚህ ጥቁር ከወለዱ ተስፋ ይቁረጡ። ጥቁር ልጅ ፈጽሞ አይፈለግም። ጥቁር ዋጋ አያወጣም። ጥቁር ልጅ ተፈለገ ከተባለ መጠርጠር ነው። ከጀርባው መከራ አለ። የጦርነት፣ የረሃብ፣ የበሽታ (የፖሊዮ)፣ የልመና፣ … ማሳያ ከመሆን አያልፍም። በዚህ ረገድ ‘ዋጋ’ ያወጣል። ቢፈልጉ “ኒውስዊክ”፣ ቢያሻዎ “ዋሽንግተን ፖስት” ካሰኞትም “ታይም” መጽሔት ‘ይገዛዎታል’። በዚህ አይጠራጠሩ። በተለይ እግሩ የተቆረጠ፣ ዓይኑ የተገለበጠ፣ ሆዱ ያበጠና ፀጉሩ የተላላጠ ከሆነ ጥሩ ማሳያ ስለሚሆን “ይፈለጋል!!!”። ነጭ ድንቡሼ ሕፃን ከነዚህ ክፉ ነገሮች ጀርባ ተቀርጾ ማየት መጥፎ ሟርት አይመስሎትም? 
... ሙሉ ፅሁፍ 
ተስፋ ላለመቁረጥ ምክንያት አይጠፋም 
ፀዳለ ክፍሌ (የንጋት ባልደረባ) 
ሰው ማኅበራዊ እንስሳ ነው ይባላል። ይህ ገጻችንም የማኅበራዊ ጉዳይ ነው። “እንስሳነቱ” እርግጥ ቢሆንም ማኅበራዊነት የታከለለት የማሰብ ችሎታው በፈጠረለት ልዕልና ነው። በማሰብ ችሎታው ተመክቶም ነው ማኅበራዊ እንስሳነቱን እራሱ ለራሱ ሰይሞ ያፀደቀው። በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ፍጡር እንደመሆኑ ክቡር ነው። ሌሎች ፍጥረታት ከሰው ሊሞግቱት እንዳይችሉ ሆነው ተፈጥረዋልና ምንም ልናደርግላቸው አንችልም። እናዝናለን! እነሱ ያዝኑልን ከሆነም አላውቅም። 
... ሙሉ ገጽ
ኦ! ፍቅር በስምሽ …? 
ፀዳለ ክፍሌ (የንጋት ባልደረባ) 
”ፍቅር፡- ሰጥቶ መቀበል ነው” የሚባል በየዘመኑ ብዙ ጊዜ ከመጠቀሱ የተነሳ ተድጦ - ተድጦ የላመ አባባል አለ። ተወቅጦ - ተወቅጦ የደቀቀ፤ ታሽቶ - ታሽቶ የተላላጠ ቢባልም ያስኬዳል። አንድ ነገር ደግሞ ያለማሰለስ ከተደጋገመ ውሸትም ቢሆን እንኳን እንደ ህዝብ መዝሙር ከጭንቅላት ተቀርጾ ይቀራል። አንዳንዴ ታዲያ ይህን የተጠቀሰውን አባባል ጠጋ ብለው ’ሲያሸቱት’ የገበያ ልውውጥ የሚመስል ጠረን ይሸተናል። በገበያ ልውውጥ ሰጥቶ መቀበል የግድ ነው። ወይም ተቀብሎ መስጠት። ቃሉ ወደ ፍቅር ሲተረጐም ደግሞ ሰጥቶ መቀበል ግዴታን አያመለክትም። በፍቅር ውስጥ ሰጥቶ ማጣት አለ። ተቀብሎ አለመስጠትም እንደዚያው። ”ውጦ ቁልጭ” ብሎ ማዳበር ይቻላል። ይህ ከሆነ ታዲያ ፍቅር ሁለት ነፍሶች የየግል ጥቅማቸውን ጥለው (ረስተው) በውዴታና በለሆሳስ የሚያደርጉት ስምምነት ነው ማለቱ ጣመኝ። አይጥምም? ሙሉ ገጽ 
ንፉግ አንደበቶች 
በፀዳለ ክፍሌ (የንጋት ባልደረባ) 
”ምን ናፈቀሽ?” በሉኝ፤ ”አበጀሽ!” የሚለኝ ሰው። እንደዚህ ባሰብኩ ቁጥር ትዝ የምትለኝ እናቴ ብቻ ነች። ለአቅመ ሔዋን ከመድረሴ በፊት ይህን ቃል የሰማሁት ከእሷ አፍ ብቻ ነው። እሷም ብትሆን ጥሩ ሥራዬ እንዲበለፅግ ፈልጋ ሳይሆን በእናትነት ፍቅር ”ጐሽ የኔ ልጅ!” ትለኝ ነበር። ለአቅመ ሔዋን ከደረስኩ በኋላ እሷም አቆመችው። የሔዋንን ኃጢያት ለመሸከም ደረስኩ ማለት ይሆን? እኔ ልሙትላችሁ ይህን ቃል ከሌላ ሰው አፍ ከሰማሁት ፴ (30) ዓመት ሞላኝ። ሙሉ ገጽ
”ቲፎዞዎች”፦ በተውሶ ነፍስ የሚኖሩ 
በፀዳለ ክፍሌ (የንጋት ባልደረባ) 
በየአቅጣጫው አቤት ባዮች በዝተዋል። አቤት ባይ ካለ አቤቱታ ሰሚም ይኖራል - ላደለው። አንዱ የአዞ ሌላው የሰው እንባ ሲያነባ መመልከቱ ደግሞ የተለመደ ሆኗል። የአዞ እንባ ግን በሰውኛ ሲተረጐም ያናድዳል። እምሽክ፣ እንክት፣ ድቅቅ አድርጐ እየበሉ ማንባት። አዞ እኮ እንዲህ ናት አሉ። ካላላመጠችና ካላመነዠገች እምባዋ ጠብ አይልም። ከአዞ ጋር የሚመሳሰል አንድ ፍጡር አለ። በገሃዱም ባይሆን በተረቱ ዓለም ”ብልጥ ልጅ እየበላ ያለቅሳል” የምንለው። ትላልቅ ሕፃናት ደግሞ አሉ፤ በዓይናቸው ሳይሆን በአፋቸው ’የሚያለቅሱ’ የራሳቸው ብልጦች። ሁሌም ከነሱ ወዲያ ሌላው ሞኝ የሚሆንባቸው። አድቅቀው በልተው ጦም አደርን ብለው በአፋቸው የሚያለቅሱ። እነዚህን ሳስብ ዘንቢል ሙሉ እንጀራ ተሸልሞ እራበኝ እያለ እንባውን እንደሚዘራ ”ለማኝ” ይታየኛል። (ለነገ ማሰብ ሌላ መልክ አለው) እንደዚህ አይነት ሰዎች አታውቁም? ሁሌም ብልጥ ነን ብለው ያምናሉ። ሙሉ ገጽ
አንተኛም!! 
በፀዳለ ክፍሌ (የንጋት ባልደረባ) 
ውድ አንባብያን ለዛሬ በዚህች ቀልድ እንጀምር። 
እናት ልጇ እየበጠበጠ ሥራ አላሠራ ይላታል። ስለዚህ መላ መታችና እንዲተኛላት ፈልጋ ”ማሙሽዬ ና! እንተኛ” ብላ አቅፋው ተኛች። እሱ ሲተኛ እሷ ለመነሳት። ነገሩ ተገላቢጦሽ ሆነና እሷን እንቅልፍ ይዟት ጥርግ ሲል አጅሬው ሕፃን ተነስቶ ውጭ መጫወት ጀመረ። አባቱ ከሥራ ሲመለስ ውጭ አገኘውና ”እናትህ የት ሄደች?” ሲል ይጠይቀዋል። ’እሣቱ’ ሕፃን ምን ብሎ መለሰ መሰላችሁ? - ”እኔን ለማስተኛት ተኝታለች”። ሙሉ ገጽ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Hosted by www.Geocities.ws

1