Textruta: Textruta: ንጋት
Textruta: አስተያየት / ትችት

Textruta:  
 
ዋና ገጽ
 
ዜና
 
ርዕሰ አንቀፅ
 
አስተያየት - ትችት
 
ፖለቲካ
 
ማኅበራዊ
 
ኪነጥበብ
 
ስደት
 
ሊንኮች
 
ጠቃሚ ሣይቶች
 
ስለእኛ
 
አድራሻችን
 
ለፈገግታ 
 
 
ምሉዕ የአማርኛ፣ የትግርኛና የግዕዝ ሶፍት ዌር 
ምስጋና ለፀጋዬ ገብራይ

 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Textruta: ለገበሬው ከልብ ከተለቀሰለት ... መድኃኒቱ ቀላል ነው 
ዮሐንስ አማኑኤል 
አለመታደል ሲነሳ ሁሌም በአዕምሮዬ የሚመላለሰው የአገራችን ገጠሬና ገበሬ ነው። ምናልባት በአንድ ወቅት የግብርና ተማሪ ስለነበርኩና በመስኩ ዲፕሎማ ስላለኝ ሊሆንም ይችላል። ግን ለዚህ ብቻ አይመስለኝም። በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ደርግ እና ኢህአዴግ ወደ ስልጣን የወጡት፣ ሌሎችም ወደ ስልጣን ተቃርበው የነበሩት "ትግላችን 85 በመቶ ለሚሆነው የአገሪቱ ገበሬ (ለዜጋችን) ነው" የሚል መፈክር አንስተው ስለነበር ነው። እንደሚገባኝ ከሆኑ ሁሉም ፓርቲዎች በገበሬው ስም የነገዱና ያስነገዱ ፍልፈሎች መሆናቸው ነው። 
አሁን አሁን ወኔው እየጠፋ ወይም እየከበደ መጣ እንጂ አንድ ሁለት ጠብመንጃ ማንገብ የሚቻል ከሆነ "ትግሌ ገበሬውን የመሬት ባለቤት ለማድረግ ነው!" ብሎ ጫካ መግባት ከ17 ዓመት ትግል በኋላም ቢሆን ምኒልክ ቤተመንግሥት አስገብቶ አልጋቸው ላይ ያስተኛል። በቃ! የስልጣን ጥም ካለብዎ እና ደፋር ከሆኑ የጥፍር መቁረጫ ላይ ያለችው ሰንጢም ብትሆን በእጅዎ ካለች ይሸፍቱና "ገበሬውን የመሬት ባለቤት አደርጋለሁ" ብለው ይነሱ! ዛሬም ገበሬው የያዘው መሬት የእሱ አይደለማ! - የመንግሥት ነው። ለመሆኑ ጫካ ለመግባት ድፍረቱ አለዎ? ... ሙሉውን ፅሁፍ አስነብበኝ
እኛ እነማነን? 
ዘላለም በእምነቱ (የንጋት ባልደረባ) 
መልሱ ግልጽ ነው። “ኢትዮጵያዊ ነን”። ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ በምትባለው አገር ስንኖር የጋራ ቤታችን ናት። በደስታዋ እንደሰታለን። በኀዘኗ እናዝናለን። አንዳንዴ ችግር የጋራ፣ ደስታ የግል የሚሆንበት ታሪካዊ አጋጣሚ ባይጠፋም። ለዚህም ቢሆን ተጠያቂዎች እኛው ነን። ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ፖለቲካዊም ሆኑ ማኅበራዊ ክስተቶች ጣታቸውን የሚቀስሩበት አቅጣጫ ግለሰብ፣ መንግሥት፣ ድርጅት፣ ቡድን፣ … እየሆነ ብዥታ ውስጥ ይከቱናል እንጂ ዓለም እኛን የሚያውቀን ኢትዮጵያውያን መሆናችንን ነው። ብዙ ምክንያት ኖሮን ለችግራችንም ሆነ ለድህነታችን እርስ በርስ ብንካሰስም ለመካሰሳችንም ተጠያቂነቱ ከራሳችን ላይ አይወርድም። በዚህ አጋጣሚ አንድ ገጠመኜን ላንሳ። ... ሙሉ ፅሁፍ
ልማት የማይመለከታቸው ቀበሌዎች 
ፀዳለ ክፍሌ (የንጋት ባልደረባ) 
በደርግ ጊዜ ‘በቀልደኝነታቸው’ የሚታወቁ አንድ ሹም ተናገሩት የተባለ ነገር ሁሌም ትዝ ይለኛል። ለአለቃቸው ሪፖርት ሲያቀርቡ ይሁን በስብሰባ ላይ ባላውቅም “በፖለቲካው በኩል ካድሬው፣ በኢኮኖሚው በኩል ደግሞ እኔ ህዝቡን ሰንገን ይዘነዋል” አሉ እየተባለ ሲነገር ነበር። ደርግ በዘመኑ ካጠፋቸው አያሌ ጥፋቶች የከፋው በቀላሉ ሊወገድ የማይችል የአስተሳሰብ ነቀርሳ ተክሎብን ማለፉ ይመስለኛል። እንደተስቦ እየተላለፈ እስከዛሬ የሚያሰቃየን እሱ ይመስለኛል። 
ከትልቁ ሹም ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ በትጋት የሚከታተሉትና የሚያነፈንፉት ነገር ቢኖር አንድ ብቻ ነበር። ለህዝብና ለአገር የሚበጅ ምን ተሠራ? ምን እንሥራ? ሳይሆን ከሌላው ዜጋ ሁሉ የተሻለና የተመረጠ ኢትዮጵያዊ አድርገው ራሳቸውን በመቁጠር ሌላው ዜጋ ለነሱ ከማጐብደድ በቀር የሚመለከተውም የሚያገባውም ነገር ያለ አይመስላቸውም ነበር። “ነበር” መሆኑ በጀን። በዚህ ሳቢያም ከመሪዎቻቸውና ከገዥዎቻችን የሚተላለፈውን የጭቆናና የጭካኔ አመራር ለማስፈፀም ብቻ የሚተጉ ነበሩ። በርግጥ ከዚህ ውጪ የሚመጣላቸውም መመሪያ አልነበረም። የሚያሾም የሚያሸልመውም ጭራቃዊ ተግባርን በትጋት መፈፀም ነበር። በየቀበሌው የተሰገሰጉት ሹማምንቶች በሙሉ በራሳቸው ህዝብ ላይ የሚወርደውን መዓት ከላይኞቹ በበለጠ ሁኔታ ጭራና ቀንድ እየጨመሩበት ሊተገብሩት ሲሯሯጡ መኖራቸው የትላንት እውነት ነው። ... ሙሉ ፅሁፍ
መበለጣችንን እንመን
ክንፈ ገብርኤል (የንጋት ባልደረባ) 
”ማርና ወተት የሚዘንብባት ኢትዮጵያ አገራችን” የሚለው አባባል እውነታነት አልዋጥ ካላቸው ተርታ ከተሰለፍኩ ሰነባብቻለሁ። ለዚህ ምክንያቴ ግልፅና ግልፅ - አንድና አንድ ነው። አገራችን ማርና ወተት የሚዘንብባት ነች እየተባለ ቢደሰኮርም ለእኔ አንዲት ቀን አዝንባልኝ አታውቅም። ዘንቦልኝም አያውቅም። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለጐረቤቶቼም፣ ለቤተሰቦቼም፣ ለማውቃቸውም፣ … በአጠቃላይ ለህዝቧ ማርና ወተት ዘንቦለት አያውቅም። ኢትዮጵያም ሆነች ማንም ስድሳ አምስት ሚሊዮን ለደረሰው የአገሪቱ ህዝብ ጠብ ያደረጉለት ነገር የለም። ”ዘንቦላቸዋል” ሊባሉ የሚችሉ ጥቂቶች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል። እነሱም ቢሆኑ ዘንቦላቸው ሳይሆን ወይ ሰርቀው ካልሆነም … ነው። ምን?፣ እንዴት?፣ ከማን?፣ … ሰረቁ? - ሌላ ጥያቄ ነው። ... ሙሉ ገጽ
ባንሰማው ይሻላል 
በካሌብ አባተ (የንጋት ብዕረኛ) 
ሰው ”ፈርዶበት” የሚፈልገውንና የሚስማማውን አይቶ የማይፈልገውንና ለዕይታው የማይጥመውን ላለማየት አቅም የለውም። አቅም አለው፣ ይችላል ማለት ከከጀልንም መፍትሔው ዓይን ከመጨፈን የሚያልፍ አይሆንም። ይህ ደግሞ መፍትሔ ሳይሆን አጉል ቀልድ ነው የሚሆነው። ከምናየው አብላጫው ቁጥር ለዕይታ የሚጐረብጥና ቀፋፊ በሆነበት አካባቢና አገር መጨፈን መፍትሔ ይሁን ካልን ቢያንስ ከቀን ውስጥ ግማሹን ሰዓት ጨፍነን መሪ ሊያስፈልገን ነው። ለክፋቱ ደግሞ ዓይን መጥፎ፣ አስደንጋጭና ቀፋፊ ነገር ለማየት መጣደፉ ነው ሌላው ምስጢር። ካጉረጠረጠ በኋላ አጥወልውሎን እስክንመለስ ይስገበገባል። ... ሙሉ ገጽ
ግብረ-ጥፉ በስም ይደግፉ 
በፀዳለ ክፍሌ (የንጋት ባልደረባ) 
በየትኛውም ዓለም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ”ሌቦች” አሉ። ጥቂት - በጣም ጥቂቱ ”የእጅ አመል” በሚለው አይነት የሚታወቁ እንደሆነ ሲነገር፤ አብዛኛው ግን ረሃብ የሚወልደው ስርቆሽ ነው። ረሃብ ደግሞ በዓለም ተዘርቷል። የብዛቱን ያህል ደግሞ ፈጣን ነው። ጊዜ የማይሰጥ ውጋት። ስለዚህ ለአጣዳፊ ጉዳይ ብዙ ”ሌባ” አለ ማለት ነው። ... ሙሉ ገጽ
አለሁ ሲሉ መሞት 
ከህዝብ ገጽታ ምን ይነበባል? 
በዘላለም በእምነቱ (የንጋት ባልደረባ)
”ታዲያስ ወገኖቼ?” 
መቼም ምላሻችሁ ”አለን!” እንደሚሆን መጠርጠር ከንቱ መሆን ነው። እግዚአብሔር ይህን አዲስ ዓመት ይባርክልንና ”አለን!” እየተባባልን መኖርን አይንፈገን። ምናባቱ! ድህነት ”እጣ ክፍላችን” ቢሆንም በሞራል መኖር ነው። ”ሰው በዳቦ ብቻ አይኖርም …” ብሏል መጽሐፉ። ይሄም አንድ መፅናኛ ነው። 
”እሺ አዲስ ዓመት (እንቁጣጣሽ) እንዴት ነበር?” 
”ጥሩ ነው!” አላችሁ አይደል? እኔ በበኩሌ አንድም ”ክፉ ነው” የሚል ሰው አላጋጠመኝምና መልሳችሁ ከዚህ አይዘልም። እውነት ለሁሉም ሰው ጥሩ ነበር እንዴ? ይህ እንኳን አያከራክርም። ይሉኝታ ያለው ጨዋ ህዝብ ቢርበውም ”አሁን በላሁ” ብሎ መግደርደር አለበት። ጥሩም ባይሆን ”ጥሩ”፣ ቢርበውም ”ጠገብኩ”፣ ቢጠማውም ”በቃኝ” ማለት የጨዋነታችን ገጽታ ነው። ባሕልም ነው። አኩሪ ባሕል። ሰው ስለራበው ብቻ መንሰፍሰፍ የለበትም። ተርቦም ቢሆን ክብሩን መጠበቅ ጨዋነት ነው። ”የሚያልፍ ቀን የማያልፍ ስም ይሰጣል” የምንለው’ኮ ለዚህ ነው። እንዲህ ባይሆን’ማ ለመኖር የሚያበቃን ”ሞራል” ከየት ይመጣ ነበር? ደግሞም ”የተለዩ ህዝቦች” የሚያሰኘን አንዱ ጥጋብንም ረሀብንም ”ሼር” አድርገን መኖር መቻላችን የማይሆንበት ምክንያት የለም። ይቅር በሉኝና አሁን አሁን ግን አንድ ነገር እየታየኝ ነው። ድህነታችንን ”ሼር” ለማድረግ የማንችልበት ደረጃ ላይ እየደረስን ያለን መሰለኝ። ነገሩ ግራ ይመስላል - አይደል? ... ሙሉ ገጽ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Hosted by www.Geocities.ws

1