Ethio Flag

 

AnbesaAnbesa

Amharic

Ethiopic Script and Language, (አማርኛ) the major written and spoken Semitic languages of historical and present-day Ethiopia.
The writing tradition of Ethiopia is one of the greatest cultural achievements in Africa.

Known as lessâna ge'ez -ልሳነ ግዕዝ- (meaning "the language of the free") or simply as Ge'ez, classical Ethiopic was used in the Aksumite royal inscriptions of the fourth century C.E., in translations made from Greek, Syriac, Arabic, and other languages, and for a vast body of original Ethiopian literature that includes stories of Christian saints and martyrs, poetry, historical chronicles, and treatises on magic, law, and medicine.

If you are interested to learn more about Amharic script and language, please viset this links<http://www.africanlanguage.com/amharic. >

 

 

Anbesa ዴ ዚ ዴ ራ ታ Anbesa

በዚህ ዓለም ጥድፊያና ውካታ ሳትበገር በርጋታ ኑር:: ከጸጥታ ሰላም ሊገኝ የሚችል መሆኑን አትዘንጋ :: ያለ አግባብ ሳትበለጥ የተቻለህን ያህል ከሰዎች ጋር ኑር:: እውነት ነው ብለህ የያዝከውን ነገር በጥሞናና በግልጽ ከመናገር ወደ ኋላ አትበል:: ሌሎች የሚናገሩትን ከመስማት አትቦዝን:: ሆነ ብሎ ለሚያዳምጣቸው ከከዳተኞችም ሆነ ከደደቦች ቁም ነገር አይትጠፋም:: ከጯሂዎችና   ከእኔ አለሁ ባዮች ራቅ፣ እንዲህ ያሉ ሰዎች መንፈስን ያውካሉና:: ራስህን ከሌሎች ሰዎች ማመዛዘን ከያዝክ ዕብሪተኛና መንፈሰ መራራ ልትሆን ትችላለህ:: ምክንያቱም ከሰዎች መካከል ከአንተ የሚበልጡም የሚያንሱም አይታጡም:: በምትሰራው ሥራ መሳካትም ሆነ በወደፈት ውጥንህ ተደሰት:: የምትሰራው ሥራ ዝቅተኛም ቢሆን የአኔ ነው ብለህ ያዘው:: በዚህ ወረቱ ተለዋዋጭ በሆነ ዘመን የሚያዋጣው የአንድ ሙያ ባለቤት ሆኖ መገኘት ነው:: ዓለም ብሽፍጥና የተሞላ በመሆኑ ገንዘብን በሚመለከት ነገር ጥንቃቄ አይጉደልህ:: ይህም ሲባል ሰው ሁሉ ክፉ ነው ብለህ በደፈናው አትገምት:: ከፍተኛ ቁም ነገር ያለው ተግባር ለመፈጸም የሚጣጣሩ ብዙ ሰዎች መኖራቸውንና ሕይወትም ብዙ ጀብዱ የሞላበት መሆኑን አትሳት:: በራስህ ተማመን:: በተለይም ፍቅር ማስመሰልን የሚጠላ መሆኑን እወቅ:: እንዲያውም ፍቅር በዘፈቀደ የሚታለፍ ነገር አይደለም:: በዚህ የመንፈስ ድርቀትና መሰልቸት የሚያጠቃው ዓለም እንደ ሜዳ ሣር ጠውልጎ የሚለመልም ፍቅር ብቻ ነው:: የወጣትነት ወራት ፍላጎትህ ብዙ ዘመን ልትጠራቀመ የሽምግልና ምክር በለዘብታ ይገዛ:: ሳታስበው ለሚያጋጥምህ መከራና ችግር ድጋፍ እንዲሆንህ የመንፈስ ጽናት ይኑርህ:: ሆኖም እንዲህ ያል ነገር ሳይደርስብኝ አይቀርም እያልክ በከንቱ ልብህ አይታወክ:: ብዙውን ጊዜ ፍርሃት የሚመነጨው ከመዳከምና ከብቸኝነት ነው:: ወግ ባለው ሁኔታ ኑሮህን መቆጣጠር አስፈላጊ ቢሆንም እንኳን፣ ራስህን ከመንከባከብ ቸል አትበል:: ከዕፅዋትና ከከዋክብት የማታንስ የዚህ ታላቅ ፍጥረት ዓለም ዝርያ ስለሆንክ፥በዚች ዓለም ላይ የመኖር መብት አለህ:: ሁኔታው ላንተ ግልጽ ሆኖ ባይታይም፤ ይህ ታላቅ ፍጥረተ ዓለም ያለ ጥርጥር ምሥጢሩ እያደር እየተገለጠ በመሄድ ላይ ይገኛል:: ስለዚህ ሕሊናህ አውጥቶ አውርዶ ከተቀበለው አምላክ ጋር ግንኙነትህ የሠመረ ይሁን:: ከትግልህና ከወደፈት ምኞትህ ጋር በዚህ ትርምስ በበዛበት ዓለም ስለምትኖር ለነፍስህ ሰላም አትንፈጋት:: ከክፋቱ ፤ ከልፋቱም ሆን ከውጣ ውረዱ ጋር ይህ ዓለም ግሩም ስፍራ ነው:: እንግዲህ ለኑሮህ እወቅበት:: ደስተኛ ለመሆን ተጣጣር::

''St. Paul Boltimore, 1692''

 

Album EthioProfile Personal Share Sport Home

Hosted by www.Geocities.ws

1