ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

«የሕዝቡን ድምፅ ለማስመለስ በትግሉ እንቀጥላለን» ዶ/ር መረራ ጉዲና

(ነፃነት ጋዜጣ ኀሙስ ነኀሴ ፭ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.)

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢህዴግ አሸናፊነት ያወጀበትን የምርጫ ድምፅ ውጤት ፈፅሞ እንደማይቀበሉት የሕብረቱ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና አስታወቁ።

የምርጫው ድምፅ ውጤት በመጭበርበሩ እና ቦርዱ በማጣራት ሂደቱም ለኢህአዴግ ወገንተኛነቱን በማሳየቱ ወደ ፍርድ ቤት መሄድ ፣ ሰላማዊውን ትግል መቀጠልና ሌሎችንም አማራጮች ሊጠቀሙ እንደሚችሉ የገለፁት ዶ/ር መረራ ነፃ ፍርድ ቤት በአገሪቱ ውስጥ ስለሌለ የተሰረቀውን የህዝብ ድምፅ ለማስመለስ ከሕዝብ ጋር በመሆን ሠላማዊ ትግሉን እንደሚቀጥሉበት አስታውቀዋል።

የብሔራዊ አንድነት መንግስት እንዲመሰረት ሀሳብ ያቀረቡት ተቃዋሚዎች ስልጣንን ለመጋራት ሳይሆን ለአገሪቱ ደህንነት ቅድሚያ ለመስጠት እንደሆነ የገለጹት ዶ/ር መረራ ኢህአዴግ የስልጣን ሥምምነቱን በተቃዋሚዎች ላይ ለማላከክ መሽቀዳደሙን አውግዘዋል። ተቃዋሚዎች የስልጣን ጥማት ቢኖራቸው ኖሮ የብሔራዊ አንድነት መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አያቀርቡም ያሉት የህብረቱ መሪ ኢህአዴግ ከአገሪቱ ደህንነት ይልቅ ለስልጣኑ ቅድሚያ መስጠቱን ኮንነዋል።

ኢህአዴግ ሳያሸነፍ አሸነፍኩ በማለቱ ሰላማዊ፣ ህጋዊና ፓለቲካዊ ትግሉ በሰፊው እንደሚቀጥል ያስታወቁት ዶ/ር መራራ የኢትዮጵያ ሕዝብ መብቱን ለማስከበር ለልጆቹም የተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት የሰፈነባት አገር ለማስረከብ ከሰላማዊ ትግል ውጭ ሌላ አማራጭ ስለሌለው ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ ለትግሉ ቆርጦ ይነሳ ዘንድ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

Hosted by www.Geocities.ws

1