ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

ኮ/ል ተስፋዬ ወ/ስላሴ እና ጄ/ል ለገሰ በላይነህ ሞት ተፈረደባቸው

(ነፃነት ጋዜጣ ኀሙስ ነኀሴ ፭ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.)

በነ ኮ/ል ደበላ ዲንሳ የዘር ማጥፋት ክስ መዝገብ የተከሰሱትን የቀድሞ ሥርዓት ባለሥልጣናት ክስ ሲመለከት የቆየው የፌዴራል 3ኛው ወንጀል ችሎት በሁለት የቀድሞ ባለሥልጣናት ላይ የሞት ቅጣት መበየኑ ተገለፀ።

በዚሁ የክስ መዝገብ የቀረቡት የሃገርና የሕዝብ ደህንነት ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩት ኮ/ል ተስፋዬ ወ/ሥላሴ እና የዘመቻ ጥበቃ መምሪያ ኃላፊ፣ የደርግ ምርመራ ኃላፊ፣ የማዕከላዊ ምርመራ ዋና ሹምና የፖለቲካ እስረኞች ውሳኔ ሰጪ ኮሚቴ አባል የነበሩት ጄ/ል ለገሰ በላይነህ በሞት እንዲቀጡ ወስኗል። በሌሎች የቀድሞ ባለሥልጣናት ላይ እንደ ጥፋት ደረጃቸው ከእድሜ ልክ እስከ አስር ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተበይኗል።

ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

Hosted by www.Geocities.ws

1