ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

«በአለም ታይቶ የማይታወቅ ቅጥፈት የተፈፀመበት ምርጫ» ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል

(ሀዳር ጋዜጣ ኀሙስ ነኀሴ ፭ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.)

ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገው ውጤት ኢፍትሃዊና በዓለም ታአይቶ የማይታወቅ ቅጥፈት የተሞላበት እንደሆነ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ኃይሉ ገለፁ።

ኢንጂነር ኃይሉ ትናንት ማምሻው ላይ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል (ኤኤፍፒ) እንደገለፁት ውጤቱ በምንም አይነት መልኩ ተቀባይነት እንደሌለውና ተጠያቂዎቹም ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ገዢው ፓርቲ እንዲሁም ምርጫ ቦርድ ናቸው ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢህአዴግ በዛሬው ዕለት አዲስ መንግስት እንደሚያዋቅር በትናንትናው ዕለት የገለፀ ሲሆን ዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው የህግ ባለሙያዎችና የፖለቲካ ታዛቢዎች ማክሰኞ ምሽት ላይ አሸናፊ መሆኑ ተገልጾለት በአንድ ቀን ልዩነት መንግስት ማዋቀሩ ቀድሞውኑ እንደተዘጋጀበት ፍትሃዊ ምርጫ እንዳልተከናወነ ያሳያል ብለዋል።

ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

Hosted by www.Geocities.ws

1