ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

«የአቶ ከማል ሁለቱም ኃላፊነቶች እርስ በርሳቸው ይጋጫሉ» ዶ/ር ይዕቆብ ኃ/ማርያም

(ሀዳር ጋዜጣ ኀሙስ ነኀሴ ፭ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.)

አንድ ግለሰብ የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበርና የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ሆኖ በየትም አገር እንደማይሾምና ኃላፊነቶቹም እርስ በርሳቸው እንደሚጋጩ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም ገለፁ።

የቅንጅት አመራር አባልና አለም አቀፍ የህግ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ያዕቆብ በትናንትናው እለት ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት መግለጫ አቶ ከማል በድሪ የጠ/ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መሆናቸውን እያወቁ የምርጫ ቦርድ አባል መሆን አልነበረባቸውም ብለዋል። ምክንያቱም ይላሉ ዶ/ር ያዕቆብ፣ ቦርዱ ላይ ባላቸው ኃላፊነት ውሳኔ የሰጡበትን ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤቱ ደርሶ ጉዳዩ በእሳቸው እጅ መግባቱ አይቀርም። በዚህ ጊዜ ሚዛናዊ ፍርድ ሊሰጡ አይችሉም ብለዋል። የህግ ባለሙያው አክለውም የምርጫውን ውጤት ተቀብሉ ብሎ ማስፈራራት ሕገወጥ ድርጊት ከመሆኑም በላይ ማስፈራራት በራሱ ወንጀል ነው ብለዋል። «ያለቅድመ ሁኔታ ተቀበል» የሚል ድንጋጌ በአለም ህግ አለመኖሩን የገለፁት ዶ/ር ያዕቆብ ፓርላማ መግባትም ሆነ አለመግባት የመብት ጉዳይ እንጂ ወንጀል አይደለም ብለዋል።

«ፓርላማ አልገባም ያለ ፓርቲ በድጋሚ አይወዳደርም» በሚል ህገ ወጥቷል ይህ ከሙያዎ አንጻር አግባብ ነው ወይ ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄም ዶ/ር ያዕቆብ ሲመልሱ አንድ ግለሰብ ወንጀል ሰርቶ ካልታገደ በስተቀር በማንኛውም ወቅት በምርጫ መወዳደር ይቻላል። መምረጥም ሆነ መመረጥ ሕገ-መንግስታዊ መብት ነው ፓርላማ አልገባም ከማለት ጋር አይገናኝም ብለዋል።

ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

Hosted by www.Geocities.ws

1