ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

የስልክ ቁጥር ዲጂት ጨመረ

(አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ ሐምሌ ፴ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.)

በአዲስ አበባ በሁሉም ዞኖች የመደበኛ ስልክ ቁጥሮች ከፊት ለፊታቸው አንድ ዲጂት የጨመረ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ በትናንትናው ዕለት ያስታወቀ ሲሆን፣ በክልሎች ለመደወል የሚያገለግለው የአካባቢ መለያ ቁጥር በአንድ ዲጂት፣ የሞባይል ስልክም በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲጨምር መደረጉንም አመልክቷል። ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባና በክልሎች ያደረገው የመደበኛና የሞባይል ስልክ ቁጥሮች ለውጥ ዝርዝር እንደሚከተው ቀርቧል።

ሀ) የመደበኛ ስልክ ቁጥሮችን ለውጥ በተመለከተ

1. ለአዲስ አበባ ከተማና አካባቢ

1.1. በሰሜን አዲስ አበባ ዞን ቴሌ ጽ/ቤት ስር የሚገኙ የስልክ ቁጥሮች ለውጥ

ለምሳሌ ቀድሞ የነበረው የስልክ ቁጥር 27-97-15 ቢሆን ከፊት ለፊቱ 1 ቁጥርን በማስቀደም 127-97-15 ይሆናል ማለት ነው።

1.2. በምዕራብ አዲስ አበባ ዞን ቴሌ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ስልክ ቁጥሮች፦

ለምሳሌ ቀድሞ የነበረው የስልክ ቁጥር 70-82-61 ቢሆን ከፊት ለፊቱ 2 ቁጥርን በማስቀደም 270-82-61 ይሆናል ማለት ነው።

1.3. በደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዞን ቴሌ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ስልክ ቁጥሮች፦

ለምሳሌ ቀድሞ የነበረው ስልክ ቁጥር 48-00-49 ቢሆን ከፊት ለፊቱ 3 ቁጥርን በማስቀደም 348-00-49 ይሆናል ማለት ነው።

1.4. በደቡብ አዲስ አበባ ዞን ቴሌ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ስልክ ቁጥሮች፦

ለምሳሌ ቀድሞ የነበረው ስልክ 49-33-07 በሆን ከፊት ለፊቱ 4 ቁጥርን በማስቀደም 449-33-07 ይሆናል ማለት ነው።

1.5. በማዕከላዊ አዲስ አበባ ዞን ቴሌ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ስልክ ቁጥሮች፦

ለምሳሌ ቀድሞ የነበረው ስልክ ቁጥር 15-26-90 ቢሆን ከፊት ለፊቱ 5 ቁጥርን በማስቀደም 515-26-90 ይሆናል ማለት ነው።

1.6. በምስራቅ አዲስ አበባ ዞን ቴሌ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ስልክ ቁጥሮች፦

ለምሳሌ ቀድሞ የነበረው ስልክ ቁጥር 62-38-26 ቢሆን ከፊት ለፊቱ 6 ቁጥርን በማስቀደም 662-38-26 ይሆናል ማለት ነው።

1.7. የአካባቢ መለያ ቁጥር

ቀደም ሲል ወደ አዲስ አበባ ከተማና አካባቢዋ ለመደወል አገልግሎት ላይ የነበረው 01 የአካባቢ መለያ ቁጥር (Area Code) ወደ 011 እንዲለወጥ ተደርጓል።

ለምሳሌ ቀደም ሲል ከሌሎች ክልሎች ይደወል የነበረው ስልክ ቁጥር 01-19-29-67 ቢሆን በአዲሱ 011-419-29-67 ይሆናል ማለት ነው።

2) በደቡብ ምስራቅ ሪጅን ቴሌ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ስልክ ቁጥሮች፦

በናዝሬት፣ በወንጂ ሸዋ፣ በአሰላ፣ በአቦምሳና በአካባቢው ከተሞች

ለምሳሌ ቀድሞ የነበረው ስልክ ቁጥር 11-12-13 ቢሆን ከፊት ለፊቱ 1 ቁጥርን በማስቀደም 111-12-13 ይሆናል ማለት ነው።

በተጨማሪም ቀደም ሲል ከሌሎች ክልሎች ሆነው ወደ እነዚህና አካባቢው ከተሞች ለመደወል የሚያገለግለው 02 አካባቢ መለያ ቁጥር (Area Code) ወደ 022 እንዲለወጥ ተደርጓል።

ለምሳሌ ቀደም ሲል ከሌሎች አካባቢዎች ይደወል የነበረው ስልክ ቁጥር 01-12-36-27 ቢሆን በአዲሱ 022-112-36-27 ይሆናል ማለት ነው።

3) በሰሜን ምስራቅ ሪጅን ቴሌ ጽ/ቤት ስር የሚገኙ ስልክ ቁጥሮችን በተመለከተ

በደሴ፣ በመካነ ሰላም፣ በወልዲያ፣ በሰቆጣ፣ በአሳይታ፣ በሸዋሮቢት፣ በሰመራና በአካባቢው ከተሞች በተጨማሪም ቀደም ሲል ከሌሎች ክልሎች ሆነው ከላይ ወደ ተጠቀሱትና አካባቢው ከተሞች ለመደወል የሚያገለግለው 03 የአካባቢ መለያ ቁጥር (Area Code) ወደ 033 እንዲለወጥ ተደርጓል።

ለምሳሌ ቀደም ሲል ከሌሎች ክልሎች ይደወል የነበረው ስልክ ቁጥር 03-24-37-50 ቢሆን በአዲሱ 033-224-37-50 ይሆናል ማለት ነው።

በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ለውጥ ተደርጓል።

ለ) ሞባይል ስልክ ቁጥሮችን በተመለከተ

በአዲስ አበባ ከተማ ከ10-25፣ ከ40-50፣ ከ60-69፣ በ84ና ከ86-89 ለሚጀምሩ 1 ቁጥርን፣ በመቀሌና በደሴ ከተሞች ከ30-31ና ከ70-72 ለሚጀምሩ 4 ቁጥርን፣ በድሬዳዋ ከተሞች ከ32-33ና ከ73-75 ለሚጀምሩ 5 ቁጥርን፣ በሻሸመኔ ከተማ በ58ና ከ82-83 ለሚጀምሩ 6 ቁጥርን፣ በጅማና ነቀምት ከተሞች በ55፣ በ57ና ከ80-81 ለሚጀምሩ 7 ቁጥርን እንዲሁም በባህር ዳር ከተማ ከ34-35 እና ከ76-77 ለሚጀምሩ የሞባይል ስልክ ቁጥሮች 8ን ከፊት ለፊታቸው በማስቀደም ለመደወል ይቻላል።

ለምሳሌ ቀድሞ የነበረው የሞባይል ቁጥር 69-25-50 ስልክ ቢሆን ከፊት ለፊቱ 1 ቁጥርን በማስቀደም 169-25-50 ማለት ነው።

በተጨማሪም ቀደም ሲል ከሌሎች ስልክ መስመሮች ወደ ሞባይል ለመደወል የሚያገለግለው 09 የአካባቢ መለያ ቁጥር (Area Code) ወደ 091 እንዲለወጥ ተደርጓል።

ለምሳሌ ቀደም ሲል ከሌሎች አካባቢዎች ይደወል የነበረው ስልክ ቁጥር 09-48-29-40 ቢሆን በአዲሱ ለውጥ 091-148-29-40 ይሆናል ማለት ነው።

ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

Hosted by www.Geocities.ws

1