ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

ጥላሁን ገሠሠ የድጋፍ ጥሪ አቀረበ

(ጦቢያ ጋዜጣ ኀሙስ ሐምሌ ፳፩ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.)

በረጅም ዘመን የሙዚቃ ሕይወቱ ለሀገሪቱ ባበረከተው አስተዋጽኦ ባለፈው ቅዳሜ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ያገኘው አንጋፋው ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ የትብብር ጥሪ አቅርቧል።

ድምፃዊው በተለይ ከጦቢያ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ከወራት በፊት በደቡብ አፍሪካ ካደረገው ከፍተኛ ሕክምና በኋላ ጤንነቱ በጣም የተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጾ፣ በአሁኑ ወቅት የጋንግሪን በሽታ ጉዳተኞች የሆኑትን ወገኖች እንዲሁም ወላጅ አልባና አቅመ ደካማ አረጋውያንን የሚረዳ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ለማቋቋም በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

"ምግባረ ሰናይ ድርጅቱን ለማቋቋም አበረታች ውጤት እየታየ ነው" ያለው ጥላሁን ድርጅቱ በአፋጣኝ እውን ሆኖ የተነሳበትን ዓላማ ያሳካ ዘንድ ሀብቴ የሚለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጐኑ እንዲቆም ጠይቋል።

ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

Hosted by www.Geocities.ws

1