ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

በአዲስ አበባ ከተማ ከ187 ሺ በላይ ፈቃደኛ ተመርማሪዎች ውስጥ 26 ሺ ሰዎች በደማቸው ውስጥ የኤድስ ቫይረስ ተገኘ

(ልሳነ ሕዝብ ጋዜጣ ዓርብ መስከረም ፯ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.)

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የጤና ድርጅቶችና የምርመራ ማዕከላት ደማቸውን ከሰጡ 187 ሺ የከተማዋ ነዋሪዎች ከ26 ሺ በላይ የሆኑት በደማቸው ውስጥ ኤድስ አምጪ ቫይረስ እንደተገኘባቸው የመዲናዋ ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያ መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ዶ/ር አሸናፊ ኃይሌ የጽ/ቤቱ ኃላፊ ሰሞኑን በአስተዳደሩ የባህል አዳራሽ በተካሄደው ጉባኤ ላይ እንደገለጡት ሻይረሱ በደማቸው ውስጥ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 14.8 ከመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

ጽ/ቤቱ 13 ሺ ለሚሆኑ ነፍሰ ጡር ሴቶች ሻይረሱ ከእናት ወደ ጽንስ እንዳይተላለፍ የሚያስችል ሕክምና ተጠቃሚ ማድረጉን የጠቆሙት ኃላፊ፣ 12.3 ሚሊዮን ኮንዶሞችን በነፃና እጅግ አነስተኛ ዋጋ ማሰራጨቱን አስረድተዋል።

ጽ/ቤቱ ኅብረተሰቡ ራሱን ለማወቅ የጀመረውን የፈቃደኝነት ምርመራ ለማበረታታት የምርመራ ማዕከላቱን ቁጥር ወደ 200 ከፍ ለማድረግና የተጠቃሚዎችንም ብዛት ወደ 500 ሺህ ለማሳደግ መታቀዱን ዶ/ር አሸናፊ ገልጠዋል።

ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

Hosted by www.Geocities.ws

1